ታራሚን ለመጎብኘት
ታራሚ በተሳካ ሁኔታ ወደ ማህበረሰቡ ዳግም እንዲቀላቀል ጎብኝዎች ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። ወደ ስቴት ተቋም ጉብኝትዎ አጋዥ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ ዓላማችን ነው።
እንዲሁም ለታራሚዎች ቤተሰብ አባላት አገልግሎት ከሚሰጥ ገለልተኛ ድርጅት የታራሚዎች ቤተሰቦችን ማገዝ (AFOI) ጋር በመተባበር የቪዲዮ ጉብኝት እድሎችን እንሰጣለን።
ስለ የጉብኝት ፖሊሲያችን ሙሉ ዝርዝሮችን የአሠራር ሂደት 851.1 ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የጉብኝት አዳዲስ መረጃዎች
የተቋም አዳዲስ መረጃዎች
Buckingham Correctional Center (በኪንግሃም ማረሚያ ማዕከል)
የቡኪንግሃም ማረሚያ ማእከል ሁሉም ጉብኝት (በአካል እና ቪዲዮ) ለላይ-ኤን (N-3 እና N-4) እና C3 እስከሚቀጥለው ማስታወቂያ ተሰርዟል።
Nottoway Correctional Center (ኖቶዌይ ማረሚያ ማዕከል)
ለተጨማሪ ማስታወቂያ ከህንጻ በስተቀር ሁሉም (በአካል እና በቪዲዮ) ሁሉም ጉብኝት ተሰርዟል።
Wallens Ridge State Prison
በ C-4 Pod ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ጉብኝቶች (በአካል-በመገኘት እና በቪዲዮ አማካኝነት የሚደረጉ) ረቡዕ፣ ጁላይ 2ዕለት የሚጀምሩ ይሆናል። የሌሎች ፖዶች ሁሉም ጉብኝቶች (በአካል-በመገኘት እና በቪዲዮ አማካኝነት የሚደረጉ) እስከ ሰኞ ኦገስት፣ 4ዕለት ድረስ እንደተሰረዙ ይቆያሉ።
አጠቃላይ አዳዲስ መረጃዎች
ከጁን 1፣ 2023 ጀምሮ ታራሚዎች በጃንዋሪ እና ጁላይ የታራሚ ጉብኝት ዝርዝርን ማጠናቀቅ እና ለአማካሪዎቻቸው ማቅረብ አይጠበቅባቸውም። ጎብኝዎች በአካል ለመጎብኘት እንዲፈቀድላቸው ከእንግዲህ በኋላ በታራሚው የተፈቀደ የጎብኝዎች ዝርዝር ውስጥ መሆን አይጠበቅባቸውም። ሌሎች የጉብኝት መስፈርቶች በሙሉ አሁንም ተፈጻሚ ይሆናሉ። ታራሚን ለመጎብኘት የሚያስችሉ መመሪያዎች በሚከተለው ክፍል ተዘርዝረዋል።
የተሻሻለው፦ ማርች 27፣ 2024
መምሪያው አንዳንድ ጎብኝዎች ViaPath የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም የቪዲዮ ጉብኝት መርሐግብር ማስያዝ እንደማይችሉ ያውቃል። ViaPath ጉዳዩን ተገንዝቦ መፍትሄ ላይ እየሰራ ነው። መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ ጎብኚዎች የቪዲዮ ጉብኝታቸውን ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር በመጠቀም ViaPath ድረ ገጽ፣ https://vadoc.gtlvisitme.com/app ላይ መርሃግብር እንዲያሲዙ ይበረታታሉ።
እንዴት እንደሚሰራ
ለጉብኝት ለማመልከት
አዲስ ጐብኚ ከሆኑ ወይም የጉብኝት መብቶችዎን የሚያሳድሱ ከሆነ በመስመር ላይ የጉብኝት ማመልከቻ ያስገቡ።
የጉብኝት መብቶችን ለማሳደስ
ሁሉም የጎብኝዎች ማመልከቻዎች ከፀደቁበት ቀን ከሦስት ዓመት በኋላ ያበቃሉ። ያልተቋረጠ የጉብኝት መብቶችን ለማስቀጠል በስቴት ውስጥ ላሉ ጐብኝዎች ጊዜው ከማብቃቱ ቢያንስ ከ45 ቀናት በፊት እና ከስቴት ውጪ ላሉ ጐብኝዎች ጊዜው ከማብቃቱ ቢያንስ ከ90 ቀናት በፊት አዲስ የተሻሻለ የጎብኝዎች ማመልከቻ በመስመር ላይ ያስገቡ።
የልጆች ማመልከቻዎች
እንደ አዋቂ ጎብኝዎች ሁሉ ታዳጊ ጐብኚዎችም ለጉብኝት ተቀባይነት ማግኘት እና መመዝገብ አለባቸው። አንድ ታዳጊ ታራሚን እንዲጎበኝ ማመልከት ከፈለጉ የእነርሱን ማመልከቻ ከአዋቂ ማመልከቻ ጋር ማያያዝ አለብዎት።
የመስመር ላይ የጉብኝት ማመልከቻውን በማጠናቀቅ ታዳጊ የመጨመር መመሪያዎችን ይከተሉ። በማመልከቻዎ ላይ ከአንድ በላይ ታዳጊዎችን መጨመር ይችላሉ።
ታዳጊዎች ከወላጃቸው፣ ከህጋዊ አሳዳጊያቸው ወይም ተቀባይነት ካለው አዋቂ ጐብኝ ጋር አብረው መሆን አለባቸው። የቅርብ ቤተሰብ የሆኑ ታዳጊዎች ብቻ ለግንኙነት ጉብኝቶች ፈቀድ ያገኛሉ። አዋቂ ጐብኝዎች ታዳጊን ለመጎብኘት በሚያመጡበት ጊዜ ሁሉ የተሟላውን በሕግ የተረጋገጠ መግለጫ ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቅጂ ማቅረብ አለባቸው። የታዳጊ ጎብኚ በሕግ የተረጋገጠ መግለጫ
ማንን መጎብኘት ይችላሉ
በርካታ ታራሚዎችን መጎብኘት የሚችሉት የቅርብ ቤተሰብዎ አባላት ከሆኑ ብቻ ነው።በአሠራር ሂደት 851.1 መሠረት የቅርብ ቤተሰብ አባላት የታራሚውን ወላጆች፣ የእንጀራ ወላጆች፣ አያቶች፣ ሕጋዊ የትዳር አጋሮች፣ የዘር፣ የእንጀራ ወይም ሕጋዊ የማደጎ ልጆች እንዲሁም የዘር፣ ግማሽ፣ የእንጀራ ወይም ሕጋዊ የማደጎ ወንድሞች እና እህቶችን ያካትታል። የማረሚያ ሥራዎች አስተዳዳሪው የአንድ ግለሰብ የቅርብ ቤተሰብ ሁኔታን በተመለከተ ይግባኝ ላይ ይወስናል። ጎብኝዎች የቅርብ ቤተሰብ አባል ያልሆነን አንድ ታራሚ ብቻ ለመጎብኘት የተገደቡ ናቸው።ቅርብ-ያልሆኑ የቤተሰብ አባላት የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ እጮኛዎች፣ ሴት ጓደኛዎች፣ ወንድ ጓደኛዎች፣ አክስቶች፣ አጎቶች፣ የአጎት ወይም አክስት ልጆች፣ ጓደኛዎች፣ አማቾች እና ጎረቤቶች።
የማመልከቻ ድጋፍ
ታራሚን ለመጎብኘት ማመልከቻ ለመሙላት እርዳታ ከፈለጉ፣ የታራሚዎች ቤተሰቦችን ማገዝ (AFOI) እንዲያነጋግሩ እናበረታታዎታለን። ማመልከቻዎ አንዴ ከተላከ በኋላ እርሱን በተመለከተ መረጃ ማግኘት አይችሉም። ስለ ማመልከቻ ሁኔታ መረጃ ለማግኘት እባክዎ ሰራተኞቻችንን ያነጋግሩ።
የጉብኝት መርሃግብር ለማስያዝ
VADOC ተቋም ውስጥ ታራሚን ለመጎብኘት ፈቃድ ካገኙ በኋላ የጉብኝት መርሃግብር አዘጋጅ ተጠቅመው በመስመር ላይ ጉብኝትዎን መርሃግብር ማስያዝ አለብዎት። አዲስ ተጠቃሚ ከሆኑ በመጀመሪያ "ዛሬ ይመዝገቡ" የሚለውን አማራጭ በመጠቀም መመዝገብ አለብዎት።
ምዝገባዎን ካስገቡ በኋላ፣ ጥያቄዎ "ተቀባይነት ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ" መሆኑን ማሳወቂያ ይደርስዎታል። ጥያቄዎ ተቀባይነት ማግኘቱን የሚያሳውቅ ኢሜይል በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ይደርስዎታል።
ተቀባይነት ካገኙ በኋላ ታራሚን ለመጎብኘት የሚችሉበትን ቀን እና ሰዓት መምረጥ ይችላሉ። ጉብኝቶች እስከ 14 ቀናት በፊት መርሃግብር ሊያሲዙ ይችላሉ። በከፍተኛው ጎብኚዎች በየሳምንቱ መጨረሻ አንድ ጉብኝት ይፈቀድላቸዋል።
ለታቀደው ጉብኝትዎ ዝግጅት ለማድረግ
ሁለታችሁም ለጉብኝት ማመልከቻ ካቀረቡ እና ጉብኝትዎን መርሃግብር ካስያዙ በኋላ እባክዎ ለአካል ጉብኝትዎ ለመዘጋጀት እንዲረዳዎ የሚከተሉትን መረጃዎች ይከልሱ።
ቀድመው ያቅዱ
እባክዎ ለደህንነት ፍተሻ ከጉብኝትዎ አንድ ሰዓት በፊት ወደ ተቋሙ ይድረሱ። በተቋሙ ውስጥ ምንም ምግብ ወይም መጠጥ አይፈቀድም እንዲሁም የሽያጭ ማሽኖችን ማግኘት አይችሉም።
ምን ማምጣት አለብዎት
በማመልከቻዎ ላይ ካለው መረጃ ጋር የሚዛመድ ቢያንስ አንድ ትክክለኛ የፎቶ መታወቂያ ማምጣት ይኖርብዎታል። ተቀባይነት ያላቸው የመታወቂያ ዓይነቶች የሚያካትቱት፦
- መንጃ ፈቃድ
- ፓስፖርት
(United States ውስጥ ለማይኖሩ ብቻ) - የውትድርና ID
- በፌደራል ወይም በስቴት ድርጅት የተሰጠ ሌላ መደበኛ የፎቶ ID
የአለባበስ ደንብ
ታራሚን በሚጎበኙበት ጊዜ ህጻናትን ጨም ሮሁሉም ጎብኚዎች የአለባበስ ደንቡን መከተል ይኖርባቸዋል። እባክዎ አንድን ተቋም በሚጎበኙበት ጊዜ የሚከተሉትን መመሪያዎች ያክብሩ፦
አልባሳቶቹ ከአንገት እስከ ጕልበት መሸፈን አለባቸው፣ ተገቢውን የውስጥ ልብስ ማካተት አለባቸው እንዲሁም ጫማ በማንኛውም ጊዜ መልበስ አለበት።
አልባሳቶቹ በምንም መልኩ ተገቢ ያልሆነ መሆን የለባቸውም፣ይህ የሚያጠቃልለው፦ ቲዩብ ቶፖች፣ ታንክ ቶፖች ወይም ሆልተር ቶፖች; መሃከለኛ፣ ጎን ወይም ጀርባ የሚያጋልጡ ልብሶች; ሚኒ-ስከርቶች፣ ሚኒ-ድሬሶች፣ ሾርቶች፣ ስኮርቶች ወይም ኩሎቶች (ከጉልበት ጫፍ ላይ ወይም ከዚያ በላይ); እንደ ሊዮታርዶች ፣ ስፓንዴክስ እና ሌጊንግዎች ያሉ ቅርፅ የሚያሳዩ ልብሶች; አሳልፈው-የሚያሳዩ ልብሶች; ገላጭ የሆኑ የአንገት መስመሮች እና/ወይም ከመጠን በላይ መከፋፈል ያላቸው የላይ ልብሶች ወይም ቀሚሶች; የወንጀለኛ ልብስ የሚመስሉ ልብሶች። ተገቢ ያልሆነ ቋንቋ ወይም ሥዕል ያላቸው ምልክቶችን ወይም አርማዎችን የያዘ።ይህ የወንጀለኞች ምልክቶችን፣ የዘረኝነት አስተያየቶችን፣ አወዛጋቢ ንግግሮችን ወዘተ ያካትታል። ሰዓቶች እና ሁሉም ተለባሽ ቴክኖሎጂዎች የተከለከሉ ናቸው (የጎግል መነፅሮችን ጨምሮ)።
አለባበስዎ ተገቢ አይደለም ተብሎ ከተቆጠረ ወደ አስተዳደራዊ ተረኛ መኮንን ይላካሉ። ከዚያም መኮንኑ ወደ ጉብኝት ክፍሉ መግባት ይችሉ እንደሆነ የመጨረሻውን ውሳኔ ይሰጣል።
ከታዳጊ ልጆች ጋር መጎብኘት
VADOC ቤተሰቦች ውጤታማ ለሆነ ጉብኝት እንዲዘጋጁ የሚያግዝ ለልጆች ተስማሚ የሆነ አጭር ቪዲዮ አዘጋጅቷል። ከታዳጊ ልጅ ጋር የሚጎበኙ ከሆነ የሚከተለው ቪዲዮ ልጅዎ በጉብኝቱ ወቅት ምን እንደሚጠብቀው ለማዘጋጀት ይረዳል – VADOC የጉብኝት ማስታወቂያዎች።
ለጉብኝት ለማመልከት
የአካል ጉብኝት
አዲስ ጎብኚ ከሆኑ ወይም የጉብኝት ልዩ መብቶችዎን ካደሱ የጉብኝት ማመልከቻ በመስመር ላይ ያስገቡ። የጉብኝት መርሐግብርን በመጠቀም በመስመር ላይ መመዝገብ ወይም ጉብኝትዎን መርሐግብር ማስያዝ አለብዎት።
የቪዲዮ ጉብኝት
አዲስ ጎብኚ ከሆኑ ወይም የጉብኝት መብቶችዎን የሚያድሱ ከሆነ በመስመር ላይ የጉብኝት ማመልከቻ ያስገቡ። የጉብኝት መርሃግብር አዘጋጅ በመጠቀም በመስመር ላይ መመዝገብ ወይም ጉብኝትዎን መርሃግብር ማስያዝ አለብዎት።
በቤት-ውስጥ የኢንተርኔት ቪዲዮ ጉብኝት
ምንም የጉብኝት መተግበሪያ አያስፈልግም። የጉብኝት መርሃግብር አዘጋጅ በመጠቀም በመስመር ላይ መመዝገብ ወይም ጉብኝትዎን መርሃግብር ማስያዝ አለብዎት።
አጠቃላይ የጉብኝት መረጃ
የተቋሙ የጉብኝት መርሐግብር
ሁሉም ተቋማት በተለምዶ ቅዳሜ፣ እሁድ እና የስቴት በዓላት ላይ ጉብኝት ይፈቅዳሉ። ይሁን እንጂ የጉብኝት አሠራሮች በተለያዩ ተቋማት ሊለያዩ እና በማንኛውም ጊዜ ሊለወጡ ይችላሉ። እባክዎ ጉብኝት ከማቀድዎ በፊት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ተቋሙን በቀጥታ ያነጋግሩ።
ተቋም ማውጫ ውስጥ የእውቂያ መረጃን ያግኙ።
እባክዎ በይፋ እውቅና የተሰጣቸው Virginia ስቴት በዓላት እንደሚከተለው መዘርዘራቸውን ያስታውሱ፦
- የአዲስ ዓመት ቀን
- የMartin Luther King, Jr. ቀን
- George Washington ቀን
- የመታሰቢያ ቀን
- Juneteenth
- የነጻነት ቀን
- የሠራተኞች ቀን
- Columbus ቀን እና Yorktown ድል ቀን
- የምርጫ ቀን
- የአርበኞች ቀን
- ታንክስጊቪንግ
- ከታንክስጊቪንግ በኋላ ያለው ቀን
- ገና
ተደራሽነት
በጉብኝት ወቅት ለአካል ጉዳተኞች ምክንያታዊ የሆነ ማመቻቸትን እናቀርባለን። የመንቀሳቀስ እክል ካለብዎ እባክዎ ከመጎብኘትዎ በፊት ማመቻቸቱ በቦታ መቅረቡን ለማረጋገጥ ተቋሙን ያነጋግሩ።
በልዩ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት የአገልግሎት ወይም መሪ እንስሳት በጉብኝት ቦታ ሊፈቀዱ ይችላሉ። እባክዎ ከመጎብኘትዎ በፊት ተገቢውን ፈቃድ ለመቀበል ወደ ተቋሙ ጥያቄ ያቅርቡ።
ተጨማሪ መረጃ የአሠራር ሂደት 851.1 ላይ ማግኘት ይችላሉ።
የሕክምና ሁኔታዎች ያሏቸው ጎብኝዎች
ነፍሰ ጡር ከሆኑ ወይም በታቀደለት የጉብኝት ቀን በኤሌክትሮኒክ ስካን መሣሪያው ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክል የህክምና ሁኔታ ካለዎ ከህክምና አቅራቢዎ ሰነድ ማምጣት ይኖርብዎታል። በህመምዎ ምክንያት በኤሌክትሮኒክ ስካን መሣሪያ ማለፍ እንደማይችሉ ሰነዱ ማረጋገጥ ይኖርበታል። ሌላ አማራጭ የፍተሻ ሂደት ይቀርብልዎታል።
መድኃኒት ይዘው ወደ VADOC ተቋም ለመግባት ማመቻችያ ለሚያስፈልጋቸው ጎብኝዎች መድኃኒቱ ከእርስዎ ጋር መቈየት እንዳለበት የሚጠቁም የዶክተር ማስታወሻ ማግኘት አለብዎ። የታቀደው ጉብኝት ከመድረሱ ቢያንስ አንድ ሳምንት በፊት መድኃኒት ይዘው ወደ ተቋሙ ለመግባት ፈቃድ ለማግኘት የተቋሙ ክፍል ኃላፊውን ወይም የተሾመውን ሰው ማነጋገር አለብዎ።