የጊዜ አሰላል
የፍርድ ዓይነት እና የተጣለበት የቅጣት ጊዜ መጠን ላይ በመመርኮዝ የአከባቢው ወይም የስቴት ባለሥልጣናት የታራሚውን የሚለቀቅበትን ቀን ይወስናሉ።
የመልካም ምግባር ፈቃድ ፍርዶች
ለፓሮል ብቁ የመልካም ምግባር ፈቃድ (GCA) ፍርዶች የሚከተሉትን ያካትታል፦
- ከጃኑዋሪ 1፣ 1995 በፊት የተፈጸሙ ከባድ ወንጀሎች
- ከጁላይ 1፣ 2008 በፊት የተፈፀሙ ቀላል ጥፋት ወንጀሎች
VADOC በአጠቃላይ ከ12 ወራት በላይ የሆነ ገባሪ ፍርድ ወይም ለፓሮል ብቁ የሆኑ GCA ፍርዶች ጥምረትን ሲቀበል የታራሚውን የአማራጭ ፓሮል ብቁነት፣ የአስገዳጅ ፓሮል መልቀቂያ እና የመልካም ጊዜ መልቀቂያ ቀናትን ያሰላል።
በጁላይ 1፣ 2008 ወይም ከዚያ በኋላ የተፈፀሙ የቀላል ጥፋት ወንጀሎች ለፓሮል ብቁ አይደሉም እንዲሁም ከሌሎች የስቴት ኃላፊነት ፍርዶች ጋር ካልተጣመሩ በስተቀር VADOC አያሰላቸውም።
GCA ፍርዶች መልካም ጊዜን የሚያገኙት በ30 የእስራት ቀናት ከ0 ቀናት እስከ 30 ቀናት መጠን ሲሆን ታራሚውው በሚያገኘው የክፍል ደረጃ የሚወሰን ነው። የመልካም ምግባር ፈቃድ ምደባ ስርዓት ተጨማሪ ዝርዝሮች Virginia ደንቦች §53.1-198; §53.1-202 ውስጥ ይገኛሉ።
ተገቢ የፍርድ ክሬዲት ፍርዶች
ተገቢ የፍርድ ክሬዲት (ESC) ፍርዶች የሚያካትቱት በጁላይ 1፣ 1995 ወይም ከዚያ በኋላ ለተፈጸሙ ከፍተኛ ወንጀሎች ነው። በአጠቃላይ ለአማራጭ ወይም አስገዳጅ ፓሮል ብቁ አይደሉም። ይሁን እንጂ በ2020 የተደነገጉ የሕግ ለውጦች ለተወሰኑ ESC ፍርዶች የፓሮል ብቁነትን ይፈቅዳሉ፣ Virginia ደንብ §53.1-165.1፣ ንዑስ ክፍሎች B እና E ላይ እንደተገለፀው።
VADOC ታራሚው የሚለቀቅበትን ቀን የሚያሰላው ከ12 ወር በላይ ESC ፍርድ ካለበት ነው። ESC ፍርዶች ላይ የሚተገበረው ተገቢ የፍርድ ክሬዲት መጠን የሚወሰነው Virginia ደንብ §53.1-202.3 ላይ እንደተገለጸው በወንጀሉ ወይም የሙከራ ጊዜን በመጣስ ዋነኛ ወንጀል ነው።
ተገቢ የፍርድ ክሬዲት–1
Virginia ደንብ §53.1-202.3፣ ንዑስ ክፍል A:1-17 ውስጥ የተገለጹ ወንጀሎች፣ በ30 የእስራት ቀናት ከ0 እስከ 4.5 ቀናት መጠን የሚያገኙ ሲሆን እንደ ተገቢ የፍርድ ክሬዲት-1 (ESC-1) ፍርድ ይለያሉ። መጠኑ ታራሚውው በሚያገኘው የክፍል ደረጃ የሚወሰን ነው።
ተገቢ የፍርድ ክሬዲት–2
ለማግኘት ብቁ የሆነ ወንጀል ያለበት ማንኛውም ፍርድ Virginia ደንብ §53.1-202.3፣ ንዑስ ክፍል B ላይ እንደተገለጸው በ30 የእስራት ቀናት ውስጥ ከ0 እስከ 15 ቀናት መጠን የሚያገኙ ሲሆን እንደ ተገቢ የፍርድ ክሬዲት-2 (ESC-2) ፍርድ ይለያሉ። መጠኑ ታራሚውው በሚያገኘው የክፍል ደረጃ የሚወሰን ነው።
ስለ ተገቢ የፍርድ ክሬዲቶች አመዳደብ ተጨማሪ ዝርዝሮች Virginia ደንብ §53.1-202.2; §53.1-202.4 ላይ ይገኛሉ።
የመልቀቂያ ቀናትን ማስላት
GCA ይሁን ESC፣ አንድን ፍርድ ለማሟላት የሚያስፈልገው የጊዜ መጠን በብዙ ተለዋዋጮች ላይ የተመሰረተ ነው። እያንዳንዱ መዝገብ ልዩ ስለሆነ የመልቀቂያ ቀናት በተናጥል ምክንያቶች ላይ በመመርኮዝ ሊሰሉ ይገባቸዋል።
እነዚያ ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ ነገር ግን በእነዚህ አይገደቡም፦
- VADOC ከመቀበላቸው በፊት በማቆያ ቤት ውስጥ ያሳለፉት ጊዜ
- የፍርድ አይነት
- ጠቅላላ የተጣለው ፍርድ
- ታራሚው የሚያገኝበት የክፍል ደረጃ(ዎች)
- በእስር ላይ ሳሉ የተፈፀሙ የዲሲፕሊን ወንጀሎች
- የጊዜ ሒሳብ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሌሎች ክስተቶች
ስጋቶችን ማቅረብ
ታራሚዎች የጊዜ ስሌት ጥያቄዎችን ወደሚከተለው ማስተላለፍ ይችላሉ፦
Virginia Department of Corrections
ATTN: Correspondence Unit/Court & Legal Section
6900 Atmore Drive
Richmond, VA 23261